Ethiopia Zare (ሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2000 ዓ.ም. March 17,2008) የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመስራች አባላት ማሰባሰቢያ ቅጽ አሁንም በድጋሚ ላልታወቀ ጊዜ ቦርዱ ተሰብስቦ ምላሽ ይሰጣችኋል ተባለ። የምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ማመላለስ ህዝቡ ሁኔታውን በንቃት እንዲከታተለው በር ከፍቷል።

 

ዛሬ ሰኞ ረፋዱ ላይ በደረሰን ዘገባ እነ አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል በቀጠሯቸው መሰረት ወደ ምርጫ ቦርድ ቢያመሩም የተሰጣቸው ምላሽ በደፈናው ቦርዱ ተሰብስቦ ምላሽ ይሰጣችኋል የሚል ሲሆን፣ ይህም ቦርዱ ከተቋቋመ ጀምሮ ለአንድ ፓርቲ የመስራች አባላት ማሰባሰቢያ ቅጽ ለመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የቦርዱን ውሳኔ የሚጠብቅ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ መሆኑን ታማኛ ምንጮቻችን ከሀገር ቤት አረጋግጠዋል።

ሂደቱን የተከታተሉ አንድ ታዛቢ እንደሚሉት "አንድነት የሚለው ስያሜ ራሱ እንደ ወያኔ ያሉ በጎሣ ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶችን ክፉኛ የሚያስደነግጥ በመሆኑ የመዝገብ ቤት የበታች ሹማምንቶች በቀላሉ ቅጹን ከመስጠት ሊታቀቡ ይችላሉ" በማለት የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

"ሁኔታው ለአንድነት ፓርቲ አመራሮችም ሆነ ለፓርቲው ጥሩ አጋጣሚ ነው" የሚሉት ሌላው ታዛቢ እንደሚሉት "የኢህአዴግ ምርጫ ቦርድ በሰንካላ ምክንያት ማመላለሱ ድርጅቱ በህዝብ ዘንድ እጅግ እንዲታወቅና የአገዛዙን ክፋት ያዘለ ሥራ እንዲጋለጥ ያደርገዋል" ሲሉ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጸዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ