Ethiopia Zare (ዓርብ ታህሳስ 30 ቀን 2002 ዓ.ም. January 8, 2010)፦ የመድረክ የስብሰባ ጥሪ ለእሁድ ጥር 9 ቀን 2002 ፍቃድ ማግኘቱ ተጠቆመ።

 

የተለያዩ ሰበቦች እየተፈለጉ ከታህሳስ 25 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣው የመድረክ ህዝባዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ቢሮ ፍቃድ የተሰጠው ሲሆን፤ ቦታውም ስብሰባ ማዕከል እንዲሆን ተወስኗል።

 

በዚሁም የእሁድ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢስዲፓ)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሕብረት (ደኢህዲሕ)፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ (ኦህኮ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን)፣ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት (ዓረና)፤ የሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ሶዲኃቅ)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዲአን)፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የተቋቋመበትን ዓላማና ተግባር ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ ያስተዋወቃል በማለት አቶ ገብሩ አሥራት ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ተናግረዋል።

 

በዚሁ በስብሰባ ማዕከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ህዝባዊ ስብሰባ የስብስቡ አመራር አካላትና ታዋቂ ግለሰቦች ንግግር የሚያደርጉበትና በምርጫ ዙሪያ የሚነሱ አወዛጋቢ ሂደቶች እንደሚነሱና መድረኩ አቋሙን በግልጽ የሚያሳውቅበት መሆኑ ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ