Robel Tekelemariam, Vancouver 2010የቶርኒዶ ሰዓቱን አሻሽሏል

Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 9 ቀን 2002 ዓ.ም. February 16, 2010)፦ በቫንኩቨሩ ዊንተር ኦኦሎምፒክ በአገር አቋራጭ የበረዶ ላይ መንሸራተት (ስኪ) ውድድር የተሳተፈው ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ሮቤል ተክለማሪያም ትላንት Feb.15/2010 በተደረገው ውድድር ተሳትፎ ከአራት አመት በፊት በቶርኒዶ ኢጣሊያ ያስመዘገበውን ሰዓት አሻሽሎ ውድድሩን ማጠናቀቁ ታወቀ።

 

ሮቤል ውድድሩን 45፤18.9 ደቂቃ አጠናቆ የወረወቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ከሆነው የስዊስ ተወላጅ በ8 ደቂቃዎች ዘግይቶ መድረሱንና በ93ኛ ደረጃ ውድድሩን ፈጽሟል። በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ለ20 አመታት ውጣ ውረዶችን ያሳለፈው ጀግናው አትሌት ሮቤል ከአሁን በኋላ ለሚመጡ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖች ችግሩ እሱ እንዳሳለፈው ረጅም አመታት የሚወስድ እንዳልሆነና ወጣቶች ወደዚህ ስፖርት ከመጡ መንገዶችን በቀላሉ ለመምራት እንደሚችል ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጿል።

ሮቤል የማይቻል ነገር የለም በረዶ ባይኖረን እንኳን በጎማ መንሸራተቻዎች በመለማመድ ሀገራችንንና ህዝባችንን ከማስጠራት አልፎ ከክረምቱ ኦሎምፒክ መቀላቀል ይቻላል የሚል እምነት እንዳለው ገልጾ ለዚህ ስፖርት (ስኪ) ፍቅር ያለውና ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወጣት ቢያገኝ በአጭር ጊዜ ከእሱ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግብ የሚችል አትሌት ለማድረግ እንደሚችል በልበ ሙሉነት ተናግሯል።

 

ሮቤል ለኢትዮጵያ ዛሬ በሰጠው ቃል ከአራት አመት በኋላ በራሽያ ለሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ሌላ ወጣት እንዲሳተፍ ከፍተኛ ምኞት እንዳለውና ለትብብር እንደተዘጋጀ ቢገልጽም አማራጭ ጠፍቶ ሀገሩን የሚወክለው እሱ ከሆነ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚዘጋጅ ቃል ገብቷል።

 

በውድድሩ ወቅት ኢትዮጵያዊያኖች ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን የሀገሩን ስም እየጠሩ ሲጮሁ በመስማቱ ከፍተኛ ብርታት እንደተሰማው የገለጸው ሮቤል በቤትም ሆነ በማንኛውም ቦታ ውድድሩን በመከታተል ደረጋፍ ለቸሩት ወገኖቹ ምስጋናውን አስተላልፏል።

 

9አመት ሳይሞላው በእናቱ ወ/ሮ የሻረግ ደምሴ ሙሉነህ የስራ ጸባይ ምክንያት ከእናት ሀገሩ ወደ አሜሪካን ሀገር የሄደው አትሌት ሮቤል አድጎ 35 አመት እስኪሞላው ዜግነቱን ሳይቀይር እንዴት እንደቆየ ላቀረብንለት ጥያቄ ሲመልስ ከ12 ዓመቱ ጀምሮ ስኪ (የበረዶላይ ሸርተቴ) መለማመድ ፍላጎት እንዳደረበትና ሀገሩን ለማስጠራት እንደተነሳሳ ገልጾ ይህንን ህልሙን እውን ለማድረግ ደግሞ ዜግነቱን መቀየር እንደሌለበት፤ የሚመጡበትንም ጫናዎች በተለይ በየሀገራቶች ለመንቀሳቀስ ይደርስበት የነበረውን ችግር መጋፈጥ ግድ እንደነበር አውስቷል።

 

ሮቤል ዜግነቱን እንዲቀይር ብዙ ግፊቶች ነበሩበት ያሉት ወላጅ እናቱ ወ/ሮ የሻረግ ደምሴ የሁል ጊዜ ህልሙ ሀገሩን ወክሎ መወዳደር ስለነበር ዜግነቱን ሳይቀይር በጽናት ቆይቷል ብለዋል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ ጠቅልሎ ከገባበት ከአራት ዓመታት በላይ ያላያቸው የእህቱ የ4፣ የ8ና የ10 አመት  ልጆች መምጣታቸው ሳይነገረው ከኒው ዮርክ ድረስ በመምጣት ውድድሩን ተከታትለዋል።

 

ሮቤል በብቸኝነት የሀገሩን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልብ የዛሬ 50 አመት ኢትዮጵያዊው ጀግና አትሌት አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የአለምን ህዝብ በማስደነቅ በሮም ላይ አሸንፎ ነበር። 

     

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ