በአንድ ራስ ሁለት ምላስ - አቡነ ጳውሎስ

Abune Paulos, አቡነ ጳውሎስ”አልተሳሳትኩም፣ ሐውልት ማሠራት በእኔ አልተጀመረም” አቡነ ጳውሎስ

”ሐውልት መሠራቱን አላውቅም፤ ሐውልቱ ሲገለጥ ነው ያየሁት” አቡነ ጳውሎስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም. October 26, 2010)፦ አዲስ አበባ ጉባዔ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ከብዙ የአባቶች ውትወታ በኋላ ስለ ሐውልታቸው ጉዳይ ዛሬ ምላሽ የሰጡት አባ ጳውሎስ፤ ሁለት የተጻረሩ ሃሳቦችን በማቅረብ መደናገር እንዲፈጠር ቢያደርጉም፤ ሲኖዶሱ ሐውልታቸው እንዲፈርስና ፖስተሮቹም ከተሰቀሉበት እንዲነሱ ወሰነ።

 

Statue of Abune Paulos, Addis Ababaበአቡነ ጳውሎስ የሚመራው ሲኖዶስ ካሳለፍነው ሣምንት ጀምሮ በተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ባለሥልጣናት ላይ ሹም ሽር በማድረግና አላግባብ ተወስነዋል በተባሉ የቤተክህነት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

 

በአባቶች ዘንድ ከፍተኛ ክርክር አስነስቶ የነበረው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት ማሠራት ጉዳይ ምላሽ ሳይሰጥበት በይደር እንዲታለፍ ቢደረግም፤ ዛሬ አባቶች ባሳዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ላለመስጠት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ፓትርያርኩ ሐውልት ማሰራት በእሳቸው እንዳልተጀመረና እሳቸውም ምንም የተለየ አዲስ ነገር እንዳላደረጉ ቢገልጹም፤ አንድ አንድ አባቶች በተቃውሞ ተነስተው ሕገ ሥርዓትን የሚጻረርና የአባቶችን ደንብ የሚቃወመው መሆኑን በተደጋጋሚ ካስረዱ በኋላ አቡነ ጳውሎስ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተናግረዋል።

 

የአባቶች ውትወታ የበዛባቸው አባ ጳውሎስም ሐውልታቸው ሲቆም ምንም እንደማያውቁና በቦታው ሲደርሱ የተሸፈነው ሐውልት ሲገለጥ ብቻ ማየታቸውን የመጀመሪያ ንግግራቸውን በሚክድ መልኩ ቢገልጹም፤ አባቶች ድርጊቱን በሚመለከት በቤተክህነት አባቶች በኩል በሚገባ እንደሚታወቅና በመገናኛ ብዙኀኖች መለፈፉን በግልጽ ከማስቀመጣቸው በላይ አቡነ ጳውሎስ ይህንን ድርጊት ተፈጻሚ እንዳያደርጉ ምክር ቢሰጡም ተቀባይነት ማግኘት አለመቻላቸውን በመመስከራቸው፤ ሲኖዶሱ የአባ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ ውሳኔውን አስተላልፏል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ