ከ97 ምርጫ በኋላ የት እንደደረሱ ያልታወቁ ዜጎች መኖራቸውን ኢሰመጉ ገለጸ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. December 9, 2010)፦ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ከረጀረም ጊዜ ቆይታ በኋላ የመብቶች ጥሰትን የሚያሳየውን 34ኛ መግለጫ ይፋ አደረገ። ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ የደረሱበት ያልታወቁ ዜጎች መኖራቸውን አትቷል።
በኢትዮጵያ ይካሄዳሉ ያላቸውን የሰው ልጆች መብት ረገጣ በአስር ክፍል በማስፈር ያጋለለጠው ይሄው መግለጫ በተለይ በምስራቅ ጎጃም በፖሊሶች ግድያ ተፈጸመባቸው ያላቸው አቶ እንግዳወረቅ አጥናፉ የስድስት ቤተሰቦች አስተዳዳሪ እንደነበሩና በጥበቃ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆናቸውም መሳሪያ ጠፍቶባቸዋል በሚል ምክንያት በፖሊሶች ከተያዙ በኋላ በተፈጸመባቸው ድብደባ ህይወታቸው ማለፉን አብራርቷል። በተያያዘም አወት ወልደ ገብርኤል የተባለ የ16 አአመት ታዳጊ ወጣትና የ6ኛ ክፍል ተማሪ በጎንደር ከተማ ጸጥታ አስከባሪ ጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉን አክሎ ገልጿል።
ምስክሮችንና የተጠቂ ቤተሰቦችን ዋቢ በማድረግ ሰመጉ ባወጣው መግለጫ በተለያዩ ቦታዎች ዜጎች ከማስፈራራት እስከ ደረሱበት አለመታወቅ የደረሱ ዜጎች መኖራቸውን አረጋግጧል። ከ97ቱ ምርጫ ጋር በተያያዘ የምርጫ ታዛቢና ቀስቃሽ ናቸው ተብለው ቢንያም በላይና ተመስገን ተስፋዬ የተባሉ ግለሰቦች ስም ጠቅሷል። መግለጫው ተፈጸሙ ያላቸውን ግድያዎች ለመሸፈን በምስክሮችና በዋቢ ማስረጃዎች ላይ በፖሊሶች የሚያደርሱትን ወከባ አልደበቀም። (የኢሰመጉን ሙሉ መግለጫ አስነብበኝ!)



