Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 22 ቀን 2000 ዓ.ም. May 30, 2008)፦ ከሐረር ከተማ 75 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ጅጅጋ ከተማ ትናንት ሌሊት በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ25 ሰዎች በላይ መሞታቸውን ከኢትዮጵያ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

 

ከጅጅጋ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኙ አካባቢዎች ትናንት ምሽት ላይ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ወደ ከተማዋ ጎርፍ ሆኖ በመግባቱ ነው አደጋው ሊደርስ የቻለው። የከተማዋ ነዋሪዎች ሌሊት በተኙበት የጎርፍ አደጋው የደረሰ በመሆኑ ጉዳቱ ሊያይል መቻሉ ታውቋል።

 

የሟቾች ቁጥር እስካሁን በውል አልታወቀም። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተራችን እንደገለጹት ከሆነ ቁጥሩ እስከ ስድሳ ሊደርስ ይችላል ብለዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን የሟቾች ቁጥር 25 ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

 

አብዛኞቹ ሟቾች ሕፃናት ሲሆኑ ከጎርፍ አደጋው 200 ሰዎች መትረፋቸው ታውቋል። በአካባቢው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አደጋው ከደረሰ በኋላ እርዳታ ለመስጠት በስፍራው መገኘቱ ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ