Ato Muluneh Eyuel"ግንቦት 7 ንቅናቄን ሊቀላቀሉ ይችላሉ"

Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. June 30, 2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የቀድሞ ፀሐፊ አቶ ሙሉነህ እዩኤል በትናንትናው ዕለት ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።

 

አቶ ሙሉነህ እዩኤል አመራሮቹ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ከኢትዮጵያ ውጭ በተደረገው ጉዞ የአውሮፓውን ቡድን ወክለው ጉዞ ያደረጉ ሲሆን፣ ከተመለሱ በኋላ ጥቂት የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ተካፍለው መቅረታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

 

አቶ ሙሉነህ የቅንጅት አመራሮች ፓርቲው ስሙን ቀይሮ አንድነት ፓርቲ እንዲመሰረት ሲወሰንና ስሙ ሲወጣ አብረው ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ በቀጣይ ግን በስብሰባ እንዲገኙ ጥሪ ሲቀርብላቸው ከአዲስ አበባ ውጭ የሚሰሩዋቸው ሥራዎች እንዳሉዋቸው በመግለጽ በተደጋገጋሚ ይቀሩ የነበረ መሆኑን የጠቀሱት እነዚሁ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አንዳንድ ጊዜ ግን ብቅ ይሉ እንደነበር ገልጸዋል።

 

በመጨረሻ አንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ለመጥራት ዝግጅት ሲያደርግ እንደማይቀጥሉ የታወቀ ሲሆን፣ በትናንትናው ዕለት ጉዞአቸውን ወደ አሜሪካ ማድረጋቸው ታውቁአል።

 

አቶ ሙሉነህ ከሦስት ሣምንት በፊት በኢትዮጵያ ጋብቻ መፈጸማቸውን ምንጮች ጠቁመው፣ በአሜሪካን አገር ቆይታቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደሚፈልጉና የዶ/ር ብርሃኑን ግንቦት 7 ንቅናቄ ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገምቷል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ