አቶ ተፈራ ደገፌ በ88 አመታችው አረፉ
"ገንዘቡ በኮሚኒስት ሀገር የሚታተም ከሆነ ስራዬን እለቃለሁ" አቶ ተፈራ ደገፌ ለደርግ ሰዎች
Ethiopia Zare አርብ የካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. March 06, 2015፦ የኢትዮጵያ ባንክ ገዥ የነብሩትና ለርዥም ዓመታት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን በሙያቸው ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ በቫንኩቨር-ካናዳ በህክምና ሲርዱ ከቆዩ ብኋላ በ88 ዓምታችው ዛሬ አርብ ማርች 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11 ሰዓት ተኩልከ (5፡30 am) ማርፋቸው ታወቀ።
አቶ ተፈራ በንጉሱ ዘመን በውጭ ሀገር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከተላኩት ጥቂት ተማሪዎች አንዱ ሲሆኑ በወቅቱ እርሳቸውና በጓደኞቻቸው ጥረት የተቋቋመው የውጭ ሃገር ተማሪዎች ህብረት የመጀመሪያውሰብሳቢ የነበሩና በቀጣይ አመት ግርማሜ ንዋይ ስልጣኑን እንደተረከበ ማስታወሻቸው ያወሳል።
አቶ ተፈራ ደገፌ የባንክ ገዥ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት በርካታ አለማቀፍ ድርድሮችን ከመንግስታትና መንግስታዊ ያልሆኑ ታላላቅ አለማቀፍ ተቋማት ጋር በማድረግ ሀገራቸው በአለማቀፍ ደረጃ እውቅና እንድታገኝ በርካታጥረቶችን ከርማድረጋቸውም በላይ ንጉሱ ጋር የመቅረብ እድል ባገኙ ቁጥር ሃገሪቱን በተሻለ ጎዳና እንድታመራ ምክር ይሰጡ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
የደርግ መንግስት ገንዘብ ለመቀየር ታስቦ በነበረበት ወቅት ገንዘቡ የኮሚኒስት ሃገራት እንዲታተም ሃሳብ በቀረበበት ወቅት አቶ ተፈራ አሳማኝ ያሉትን ሃሳብ ካቀረቡ ብኋላ ይህ እሳቸው በስራ ላይ እያሉ ሊሆን እንደማይችልና መልቀቂያ እንዲሰጣቸው እስከመጠየቅ እንደደረሱ ለዚህም ሊቀምንበር መንግስቱ ጋር ቀርበው ሊቀመንበሩን በማሳመን እንግሊዝ ሃገር እንዲታተም ከማድረጋቸውም በላይ ምስጢሩ ሊቀ መንበሩን ጨምሮ 5 ሰዎች ብቻ እንዲያውቁት በማድረግ በከፍተኛ ምስጢር የገንዘብ ቅየራውን አንደፈጸሙ ይታወቃል። ገንዘቡ ሲታትም በአዲሱ የኢትዮጵያ ብር ላይ ፊርማቸው እንዲቀመጥ የተደርገ ቢሆነም ገንዘቡ በታተመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ እስር ቤት መጣላቸው ለብዙዎች መደናገርን ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
አቶ ተፈራ ደገፌ በካናዳ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚሰሩ ሁለት ልጆቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመጭው ማክሰኞ ጠዋት የፍታት ስነስርአት በምስካ ኅዙናን መድኀኒአለም እና ጸደንያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተደረገ በኋላ የቀብር ስነስርአታቸው እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ለመላ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!



