አዲስ አበባ የሚገኝ ቤታቸውን ለፌስቱላ ሆስፒታል ለግሰዋል
Ato Tefera Degefes funeral የአቶ (ዶ/ር) ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመ

Ethiopia Zare ማክሰኞ መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓም March 10, 2015፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ፤ የኢትዮጵያን የባንክ አገልግሎት ስርአት ካሳደጉት ሰዎች አንዱ የሆኑትና በመድህን ድርጅት፤ በሲቪል አቪየሽንና በተለያየ ሀላፊነት ሀገራውንና ህዝባቸውን ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ (ዶክተር)፤ የቀብር ስነ-ስርአት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 1 ቀን፤ 2007 ዓ.ም. በቫንኩቨር ካናዳ ተፈጸመ።

የአቶ ተፈራ አስከሬን፤ ልጆቻቸው፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ካናዳውያን በተገኙበትና የረዥም ዘመናት የትዳር ጓደኛቸው (ባለቤታቸው) አስከሬን ባረፈበት በቫንኩቨር mountain view መካነ መቃብር፤ አርፏል።

Ato Tefera Degefes funeral የአቶ (ዶ/ር) ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመ

ስርአተ ፍትሀታቸው፤ በአቶ ተፈራ ደገፌ ኑዛዜ መሰረት፤ አባል በሆኑበትና የ84ኛ አመት የልደት በዓላቸውን ለማሰብ የተሰባሰቡ ምእመናን በጀመሯት፤ የቫንኩቨር ምስካየ ህዙናን መድሃኒያለም እና ጸድንያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተደረገ ሲሆን፤ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪና ሊቀ ዲያቆን፤ እንዲሁም ከዋሽንግተን ሲያትል በመጡ አባቶችና መነኮሳት ተፈጽሟል።

አቶ ተፈራ ደግፌ በ1966 አብዮት ማግስት ከ6 ዓመታት በላይ በእስር የቆዩ ሲሆን፤ በአስራቸው ወቅት፤ ከነአቡነ ቴዎፍሎስ ጋር እንደነበሩ በመጽሃፋቸው ታትቷል፡፡ አቶ ተፈራ ደግፌ፤ በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ የሆኑት የአቡነ መልከጸዴቅ ወዳጅ ሲሆኑ፤ በህመም ሆስፒታል የከረሙት አቡነ መልከጸዴቅ በአቶ ተፈራ ደግፌ ሞት እንዳዘኑ ተነግሯል።

Ato Tefera Degefes funeral የአቶ (ዶ/ር) ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመበአቶ ተፈራ ደግፌ የቀብር ስነስርአት ላይ የቫንኩቨር የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ብስራት ሌንጫ ንግግር ያደረገ ሲሆን፤ ልጃቸው አቶ በላይነህ ተፈራም የአባቱን ትውስታ በንግግሩ አካቶ በስነ ስርአቱ ላይ ለተገኙ እንግዶች ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

የአቶ ተፈራ ደገፌ የቅርብ ወዳጅ የሆኑትና ከ30 ዓመት በላይ በወዳጅነት የዘለቁት አቶ (ኢንጂነር) ገብረህይወት ልብሰቃልም የወዳጃቸውን ታታሪነትና ከኢትዮጵያ እስከ አፍሪካ እንዲሁም እስከ ካናዳ የዘለቀ ትውውቃቸውን በማስታወስ ስራዎቻቸውን ዘክረዋል።

አቶ ተፈራ ደግፌ፤ በአዲስ አበባ የሚገኝ መኖሪያ ቤታቸውን በአዲስ አበባ ለሚገኘው የፌስቱላ ሆስፒታል እንደተናዘዙ ለማወቅ ተችሏል።

ላለፉት አራት ቀናት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ጳጳሳት በቀብር ስነስርአቱ ላይ እንዲገኙ ጥረት ቢደረግም፤ የሲያትሉ ጳጳስ ሱባኤ ላይ ነን በሚልና፤ የካልጋሪው ጳጳስ ፍትሀቱ እኛ በፈለግነው ስፍራ ካልተደረገ በሚል ሰንካላ ምክንያት በቀብሩ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

ጳጳሳቱ በቀብሩ ስነስርአቱ ላይ እንዲገኙ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች ጳጳሳቱ በኚህ ታላቅ ሰው የመጨረሻ ስንብት ላይ ላለመገኘት በደረደሩት ሰንካላ ምክንያት ማዘናቸውን ገልጸዋል። አክለውም በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በየስድስት ወሩ ተደጋጋሚ መግለጫ ከማውጣት በዘለለ ህብረተሰቡን በሚመለከቱ መሰል ክስተቶች ላይ ስራው መታየት አለበት ብለዋል።

Ato Tefera Degefes funeral የአቶ (ዶ/ር) ተፈራ ደገፌ የቀብር ስነ-ስርዓት በቫንኩቨር ተፈጸመ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ