Bereket Simon, አቶ በረከት ስምኦን

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ March 13, 2015)፡- የመጀመሪያው ዙር የምርጫ ክርክር እንዲያደርጉ የተመረጡት አቶ በረከት ስሞኦን ከምርጫ ክርክሩ እራሳቸውን ማግለላቸው ተረጋገጠ። አቶ በረከት ለዚህ የሰጡት ምክንያት እንደሌለ ታውቋል።

ኢህአዴግ ለመጀመሪያው ዙር የምርጫ ክርክር በቂ አይደሉም እና ያሳፍሩኛል ያላቸውን ዘርዝሮ በማውጣት ውስን የሆኑ ተከራካሪዎችን ብቻ መምረጡ ታውቋል። ከሁለተኛው ዙር ክርክር ከሚያደርጉት ደግሞ እንደዚሁ በመምረጥ ገለጻ እንዲሰጣቸው አድርጓል።

በዚህ መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚጀመረው የፓርቲዎች ክርክር ላይ በአንድ መድረክ 5 ፓርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በዘጠኝ መድረኮች ክርክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በዚህ እንዳለ በዘንድሮው ምርጫ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢ ቡድን ዋጋ የሌለውን ምርጫ ለመታዘብ እግሩን እንዳማያነሳ እና ጉልበቱን እንደማያባክን መናገሩን አንዳንድ የዜና አውታሮች ዘግበዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ