Multicolored FlowersEthiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. July 26, 2008)፦ ነገ እሁድ ሐምሌ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. (ጁላይ 27, 2008) በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ “የተቅለመለሙ አበቦች” የተሰኘው የዶክተር ፍቅሬ ቶሎሣ ፊልም ለህዝብ ዕይታ ይቀርባል። 

 

ፊልሙ ምፀታዊ እንደሆነና ጥቁሮችንና ነጮችን በሚመለከት በጊዜ ሁኔታዎች እየተቀየሩ መምጣታቸውን ይንፀባረቅበታል። ድሮ ጥቁሮች ለመኖር ሲሉ ነጮችን ለመምሰል ይሞክሩ እንደነበርና አሁን ግን ነጮች ጥቁሮችን ለመምሰል እየሞከሩ እንዳለ ፊልሙ ያመላክታል።

 

በካሊፎርኒያ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት (3:00 PM) በአይሁዶች ማኅበረሰብ ማዕከል (ጂዊሽ ኮምዩኒቲ ሴንተር) በሚደረገው ዝግጅት ላይ የወጣት መቅደላዊት ታደሰ የአንድ ሰዓት ጥናታዊ ፊልም እንደሚቀርብ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። የወጣት መቅደላዊት ፊልም “ኢሚግራንት” የተሰኘ ሲሆን በአሜሪካን ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ያጠነጠነ መሆኑ ታውቋል።

 

ከዚህም በተጨማሪ “ፀሐይ ትወጣለች” በሚል ርዕስ ገጣሚ አስፋወሰን ዓለምሰገድ በቅርቡ ያሣተመውን የግጥም መድብል መጽሐፍ ያስመርቃል። ይህንን ከወትሮው ለየት ያለ የኪነጥበብ ዝግጅት በሎስ አንጀለስና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይሳተፉ ዘንድ መጋበዛቸውን ለማወቅ ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ