Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥር 13 ቀን 2000 ዓ.ም. Jan,22,2008):- ወያኔ/ኢሕአዴግን ወክለው ከደቡብ ህዝቦች ተወክለው ፓርላማ ከገቡት ተመራጮች አንዱ የሆኑት አቶ ክፍሌ ደቦባ ለአፈ ጉባኤው በጻፉት ደብዳቤ ከፓርላማ ራሳቸውን ያገለሉ መሆናቸውንና አባልነቴን አልፈልግም ማለታቸውን ታማኝ ምንጮች ገለጹ።

ተመራጩ ፓርላማውን አልፈልግም በማለት ጥለው በመውጣት የመጀመሪያው የኢህአዴግ ተመራጭ ሲሆኑ ፓርላማውም ጠያቄያቸው ተፈጻሚ እንዲሆን ያደረገ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ሁኔታው የወያኔን አገዛዝና የፖለቲካ ሂደት እርቃኑን ያወጣ ነው የሚሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች ራሳቸውን ከእርስ በርስ ንትርክ አጽድተውና ራሳቸውን በመቻቻል ተመክሮ ውስጥ አስገብተው የወያኔን አካሄድ የሚቃወሙ የወያኔ አባላትን መሄጃ እንዳያጡ ማድረግና መማረክ ጊዜው የሚጠይቀው የማያሻማ ጥያቄ ነው። በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ