Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፩ (1) ቀን ፳፻፩ (ለ2001) ዓ.ም. September 11, 2008)፦ በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር መስከረም ፩ (1) ቀን ፪፻፩ (2001) ዓ.ም. ተጀምሯል። እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማትዮስ በሠላም አሸጋገርዎ! አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የብልጽግና፣ ... ከነቤተሰብዎ ይሁንልዎ! ... በአዲሱ ዓመት በኢትዮጵያችን ዲሞክራሲ፣ ሠላም፣ ፍትህ፣ ... ይሰፍን ዘንድ፤ የዜጎች ሰብዓዊ መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ ... ይከበር ዘንድ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከችግር፣ ከችጋር፣ ከረሃብ፣ ከሰቆቃ፣ ከስደት፣ ከእስር፣ ከስቃይ፣ ከመንገላታት፣ ከድብደባ፣ ከግድያ፣ ... ይድን ዘንድ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምኞት ነው።

 

ከተጀመረች ስምንት ወራትን ያስቆጠረችው ”ኢትዮጵያ ዛሬ” ድረ ገጽ በአዲሱ ዓመት በተጠናከረ መልኩ የተጣራ፣ እውነተኛ፣ ሚዛናዊ፣ ... ዘገባዎችን ለማስነበብ የበኩሏን ጥረት ለማድረግ ትጥራለች። አንባብያንም/ትም ሃሳባችሁን በነፃነትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ትገልጹ ዘንድ የተለመደ ጥሪያችንን በዚህ አጋጣሚ ልናስተላልፍ እንወዳለን።

 

- ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ

መስከረም ፩ (1) ቀን ፪፻፩ (2001)ዓ.ም. (September 11, 2008)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ