Taye Bogale

መምህር ታዬ ቦጋለ የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው

ገዳይ መንጋዎችንና መሰሪ መሪዎቻቸውን የኢትዮጵያ አምላክ እንዴጤዛ ያረግፋቸዋል!

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 27, 2019)፦ መምህርና የታሪክ ምሁር የኾኑት ታዬ ቦጋለ የተመረዙ መስሎ እንደሚሰማቸው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ትናንት ጠዋት አስታወቁ።

መምህሩ አንድም የመድሃኒት እንክብል ወይም መርፌ በሕይወታቸው ወስደው እንደማያውቁና አሁን በማያውቁት ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት ያህል ጤንነቴ እጅግ አስጊ ደረጃ ደርሷል ሲሉ ተናግረዋል።

በሕይወቴ ሳለሁ ለቤተሰቤ አላንስም፤ ካለፍኩ በኋላ ግን ቤተሰቤን አደራ በማለት አደራውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሠጡት ታዬ ቦጋለ፤ ጠላቶቼ ቢበዙም በግል በድያቸው ሳይሆን፤ ለኢትዮጵያ ብዬ ነው ሲሉ ጽፈዋል።

ውያኔንና የጀዋር ቡችሎችን አልፈራም፤ ለዚሁም ምስክሬ ፈጣሪ ነው፤ ፊት ለፊት መጥተው በተደጋጋሚ አሸማቅቈአቸዋለሁ።

የደሱ ኦዳን ጀግንነት ማንም ይንገራችሁ፤ ቦጋለ አረጋ ገመቹ ለአገር የተዋደቀ ጀግና ነው። የዘመናት ጀግንነት፣ የአበው ወኔ ውስጤ አለ። ገዳይ መንጋዎችንና መሰሪ መሪዎቻቸውን የኢትዮጵያ አምላክ እንዴጤዛ ያረግፋቸዋል፤ ብሞትም የናንተም ሞት ይዘገያል እንጂ አይቀርም፣ ከቶም ለቅስፈት አልፈራም። ፈሪዎች በማላውቀው መንገድ መጡ፤ በየቀኑ እየተመርዘኩ ነው። አገሬ ዛሬ ብሞትልሽ እመርጣለሁ ብለው ጽሑፋቸውን በመቀጠል፤ አሁን ባለሁበት ሁኔታ የገንዘብ ድጋፍ ላድርግልህ የሚለኝ ቢኖር ጠላቴ ነው፤ መቀበሪያዬንም ጭምር አልቸገርም፤ ከእረፍቴ በኋላ ባለቤቴንና ልጆቼን አደራ ብለዋል።

ትናንት ከምሳ ሰዓት በኋላ በዚሁ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ ሐኪም ቤት መሔዳቸውንና መርፌና መድኃኒት ያገኙ መኾናቸውን ገልጠዋል። አያይዘውም ጤናቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና እጅግ በጣም ደህና መኾናቸውን ለሕዝብ አሳውቀዋል።

መምህር ታዬ ቦጋለ በቅርቡ “መራራ እውነት” የሚል መጽሐፍ ለንባብ ያበቁ ሲሆን፣ ታሪክን አዛብተው የፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አንዳንድ ወገኖችን ሽንጣቸውን ገትረው በመረጃና በማስረጃ በመከራከር የሚታወቁ የታሪክ ምሁር ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ