የአይኤምኤፍ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለመሥጠት ያቀደውን የ2.9 ቢሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ
የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF)
308.4 ሚሊዮን ዶላሩን በቅርቡ ይለቀቃል
ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 21, 2019)፦ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያ ለማበደር ቃል ገብቶ የነበረውን የ2.9 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሠጥ የሚያረጋግጠውን ውሳኔ አጸደቀ።
ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንደሚውል ታስቦ ከድርጅቱ የተፈቀደውንና በረዥም ጊዜ የሚከፈለውን ብድር ሊትዮጵያ እንዲሠጥ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ያጸደቀው ትናንት ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።
ይህንን ውሳኔውን ዛሬ ባስታወቀበት የድርጅቱ መረጃ ከተፈቀድው 2.9 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 308.4 ሚሊዮን ዶላሩ ቀደም ብሎ በቅርቡ እንደሚሠጥ ታውቋል።
ድርጅቱ የፈቀደው የገንዘብ መጠን ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ካገኘችው ጋር ተመጣጣኝ ነው። (ኢዛ)



