ልማት ባንክ የተበላሸ ብድሩን ከ40 ወደ 34 በመቶ ማውረዱን ገለጸ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
በአራት ዓመት ውስጥ የተበላሸ ብድሩን 10 በመቶ ለማድረስ አቅዷል
ኢዛ (ሐሙስ የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 27, 2020)፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበላሸ የብድር መጠኑን ከ40 በመቶ ወደ 34 በመቶ ያወረደ መኾኑን ዛሬ የባንኩ ባለሥልጣን በሠጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠን በየዓመቱ ለመቀነስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ መኾኑንና በአራት ዓመት ውስጥ ወደ 10 በመቶ ለማድረስ እየሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።
ባንኩ አምና 740 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አስመዝግቦ የነበረ ሲሆን፤ ዘንድሮ ግን በግማሽ ዓመት ከግብር በፊት ከ950 ሚሊዮን ብር በላይ በማትረፍ ከኪሳራ መውጣቱንም ገልጸዋል። (ኢዛ)



