በምርጫ ዋዜማ ምርጫ ቦርድ ዓርማውን ቀየረ
ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ የተቀየረው አዲሱ የምርጫ ቦርድ ዓርማ
“ዓርማው ግልጽነትና ተዓማኒነትን የሚያሳይ ነው” ቦርዱ
ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 14, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔርዊ ምርጫ ቦርድ ከምሥረታ ጊዜው ጀምሮ ሲጠቀምበት የቆየውን ዓርማ በአዲስ መተካቱን በመግለጽ አዲሱን ዓርማ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ እንዳስታወቀው ዓርማው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አደረጃጀት እያከናወን ያለውን ተቋማዊ ግልጽነትና ተዓማኒነትን የሚያሳዩ እንዲሁም ማንነትንና ለውጥን የሚወክሉ መገለጫዎችን ያካተተ ኾኖ የተዘጋጀ ነው ብሏል።
ይህንን አዲስ ዓርማ ዛሬ በምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ ላይ አስተዋውቋል። (ኢዛ)




