የምስክር ወረቀት

ለኦነግ የተሠጠው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

ኦነግ ለምርጫ ቦርድ ምስጋና አቀረበ

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 15, 2019)፦ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ለኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የእውቅና የምስክር ወረቀት እንደሠጣቸው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ኅዳር 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው ለሁለቱ አገር አቀፍ ፓርቲዎች የእውቅና ሰርትፊኬቱን (የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት) የሠጣቸው ትናንት ኅዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

ለኦብነግ የተሠጠው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት

ኦነግ የእውቅና ሰርትፊኬቱን ማግኘቱን ተከትሎ በሠጠው መግለጫ፤ በአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተጫወተ ላለው ሚና ምስጋና አቅርቧል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ