Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም ፲ (10) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 20, 2008)፦ ሰሞኑን በሐዋሳ በተካሄደው 7ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ለድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚነት ከመረጣቸው 36 አባላት መካከል አንድ ሴት ብቻ መምረጡ ፓርቲው ለሴቶች ተሳትፎ የሰጠውን አነስተኛ ግምት እንደሚያሳይ አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ።

 

ጉባዔው በተጠናቀቀ ማግስት አነጋገሪ የሆነው ይኸው ጉዳይ ግንባሩ እንደወትሮው ሁሉ አዲስ ነገር ያመነጫል ተብሎ ባይጠበቅም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ፓርቲውን ለሥራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ ከመረጣቸው 36 አባላት መካከል ከኦህዴድ ወ/ሮ አስቴር ማሞን ብቻ አካትቶ ጉባዔውን አጠናቅቋል።

 

ሴቶችን ለውሳኔ ሰጪነት ለማብቃት ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የሚጠቅሰው ኢህአዴግ በዘንድሮው የሥራ አስፈፃሚ ምርጫው በርካታ ሴቶች ይካተታሉ ተብሎ ሲጠበቅ፤ አንዲት አባል ብቻ መምረጡ ደጋፊዎቹንና አባላቱን አጉረምርሟል።

 

ለግንባሩ ሥራ አስፈፃሚነት የተመረጡ ኮሚቴዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፡-

 

1. አቶ መለስ ዜናዊ (ህወሓት)

2. አቶ ስዩም መስፍን (ህወሓት)

3. አቶ አባይ ፀሐዬ (ህወሓት)

4. አቶ ፀጋዬ በርሀ (ህወሓት)

5. አቶ አባዲ ዘሙ (ህወሓት)

6. አቶ አርከበ እቁባይ (ህወሓት)

7. አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ (ህወሓት)

8. አቶ አባይ ወልዱ (ህወሓት)

9. ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ህወሓት)

10. አቶ አዲሱ ለገሠ (ብአዴን)

11. አቶ ደመቀ መኮንን (ብአዴን)

12. አቶ በረከት ስምዖን (ብአዴን)

13. አቶ ተፈራ ዋልዋ (ብአዴን)

14. አቶ አያሌው ጎበዜ (ብአዴን)

15. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው (ብአዴን)

16. አቶ ተፈራ ደርበው (ብአዴን)

17. አቶ ታደሰ ካሳ (ብአዴን)

18. አቶ ብርሃን ኃይሉ (ብአዴን)

19. አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ (ደኢህዴግ)

20. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ (ደኢህዴግ)

21. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ (ደኢህዴግ)

22. ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም (ደኢህዴግ)

23. አቶ ታገሰ ጫፎ (ደኢህዴግ)

24. አቶ አለማየሁ አሰፋ (ደኢህዴግ)

25. አቶ ብርሃኑ አዴሎ (ደኢህዴግ)

26. አቶ መኩሪያ ኃይሌ (ደኢህዴግ)

27. አቶ ሬድዋን ሁሴን (ደኢህዴግ)

28. አቶ አባዱላ ገመዳ (ኦህዴድ)

29. አቶ ግርማ ብሩ (ኦህዴድ)

30. አቶ ኩማ ደመቅሳ (ኦህዴድ)

31. አቶ ጁነዲይን ሳዶ (ኦህዴድ)

32. አቶ ሙክታር ከድር (ኦህዴድ)

33. ወ/ሮ አስቴር ማሞ (ኦህዴድ)

34. አቶ ዘላለም ጀማነህ (ኦህዴድ)

35. አቶ ሶፊያን አህመድ (ኦህዴድ)

36. አቶ ዲርባ ኩማ (ኦህዴድ) ናቸው።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ