አቶ ዮሐንስ ቧያለው

አቶ ዮሐንስ ቧያለው፤ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ኾነው ተሾሙ

የሕወሓቱ ነባር አባልም ተሹመዋል

ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 25, 2020)፦ ባለፈው ሳምንት ከአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው ለቅቀው በፌዴራል ደረጃ እንደሚሾሙ ሲጠበቁ የነበሩት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፤ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ኾነው ተሾሙ። የሕወሓቱ ነባር አባል ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ደግሞ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመኾን ተሹመዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተሾሙት የሁለቱ ሹመት ይፋ የኾነው በዛሬው ዕለት የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከአማራ ክልል ምክት ፕሬዝዳንትነት ባሻገር በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንደነበሩ ይታወሳል።

ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ነባር የሕወሓት አባል ሲሆኑ፣ በተለያዩ የመንግሥትና የክልል የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩ ናቸው።

በኃላፊነት ከቆዩባቸው ውስጥ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኾነው መሥራታቸው ይጠቀሳል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ