ዐረብ ሊግ

የዐረብ ሊግ አባል አገራት

ጭፍን ውሳኔ በመኾኑ እንደማትቀበለውም ገልጻለች

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 6, 2020)፦ የህዳሴ ግድብን በመተመለከተ የዐረብ ሊግ ግብጽን በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሐሳብ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ውድቅ በማድረግ፤ ውሳኔውን ጭፍን ብሎታል።

በዐረብ ሊግ ውሳኔ ዙሪያ ዛሬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ የዐረብ ግብጽ በግድቡ ላይ የምትይዘውን አቋም እንደግፋለን በማለት ያሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ፤ ሲደረጉ የነበሩ ድርድሮችን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና ጭፍን ድጋፍ እንደኾነ ጠቅሷል።

ዐረብ ሊግ እንዲህ ያለውን የውሳኔ ሐሳብ ያሳለፈው ረቡዕ የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ሲሆን፤ ይህንን የዐረብ ሊግ የውሳኔ ሐሳብ ሱዳን ተቃውማለች። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ