አቶ እስክንድር ነጋና አቶ ማሙሸት አማረ

የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋና የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ

ለጥምረታቸው “ባልደራስ መኢአድ” የሚል ሥያሜ ሠጥተዋል

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 6, 2020)፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በማድረግ፤ በጋራ የሚታገሉበትን የፓርቲ ስያሜም “ባልደራስ መኢአድ” ፓርቲ እንዲኾን በመወሰን ተፈራረሙ።

ሁለቱ ፓርቲዎች ይህንን የጋራ ስምምነት ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ፊርማ ዛሬ የካቲት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. አኑረዋል። በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው ሰነድ ላይ ፓርቲዎቹን በመወከል የፈረሙት የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋና የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ናቸው።

ፓርቲዎቹ በቅንጅት ለመሥራት የተስማሙበት ዋነኛ ምክንያት በቀጣዩ ምርጫ 2012 በአገር አቀፍ ደረጃ አማራጭ የሚኾን የፓርቲዎች ስብስብ መፍጠር አስፈላጊ በመኾኑ ነው ተብሏል።

ስምምነቱን ተንተርሶ በተሠጠው ተጨማሪ ማብራሪያ፤ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉና በምርጫው ወቅት በጋራ ስያሜና ምልክት ለመወዳደር፤ እንዲሁም የጋራ ማኒፌስቶ ማዘጋጀትን ሁሉ ያጠቃለለ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ