የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅይላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅይላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ዶ/ር ዐቢይ በኮሮና ቫይረስ የከፋ ነገር ቢገጥመን እንኳን መዘጋጀት አደጋውን ይቀንሰዋል አሉ

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 26, 2020)፦ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመንግሥት የወጡ መመሪያዎችና እርምጃዎች በአግባቡ እየተተገበሩ አለመኾኑን ዛሬ አዲስ አበባን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ገልጸዋል።

ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረጉት ጉብኝት፤ እርምጃዎችና መመሪያዎችን ለመተግበር ገና ብዙ ይቀረና በማለት ተናግረዋል።

በፌስቡክ ገጻቸው እንደጠቆሙትም፤ “የሚጠጋን ቫይረስ የለም ሲሉ የነበሩ ያሉበትን እያየን አንዘናጋ” ብለዋል። አያይዘውም፤ ምርመራ በብዛት ባለመደረጉ ትክክለኛውን ሁኔታ አላየንምና፤ በአገር ደረጃ ተቀናጅተን መዘጋጀት አለብን በማለት ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከቅትር በኋላ በፌስቡክ ገጻቸው የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ችግር ተቋቁሞ በድል አድራጊነት ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

“የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢደርስ እንኳን ተዘጋጅተን መቆየታችን ይቀንሰዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም የገንዘብና ሌሎች አቅርቦቶችን የማሰባሰብ ሒደትን ለመተግበር ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ መዋቀሩን አስታውሰዋል።

መከራ በገጠመን ጊዜ በአብሮነት እንደምንጋፈጠው በተግባር እናሳይ ያሉት ዶ/ር ዐቢይ፤ “ኢትዮጵያ ብለን ለምንጠራት የጋራ ቤታቸን እያንዳንዳችን አስተዋጽኦና ኃላፊነት አለብን” በማለት፤ አሁን ኮሮና ቫይረስን በፌዴራልና በክልል ደረጃ እየተሠሩ ያሉትንና ሊሠሩ የታቀዱትን ሥራዎች በዚሁ መልእክታቸው ጠቅሰዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!