ሼህ መሐመድ አል-አሙዲን ለአዲስ አበባ 120 ሚሊዮን ብር ሠጡ
ሼህ መሐመድ ሑሴን አል-አሙዲ
የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ደግሞ 20 ሚሊዮን ብር ለአገር አቀፉ ኮሚቴ ድጋፍ ሠጥቷል
ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 31, 2020)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚያስፈልገው ፋይናንስ ሼህ መሐመድ ሑሴን አል-አሙዲ የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ።
አስተዳደሩ እንዳስታወቀው ሼህ መሐመድ አል-አሙዲ ያደረጉት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚያስፈልጉ ለሕክምና የሚውሉ የእጅ ጓንቶች፣ የፊት ማስኮች፣ ለለይቶ ማከሚያ ማዕከሎች የመከላከያ ጋዋኖችና ለተለያዩ የሕክምና ዕቃዎች ግዥ ይውላል።
ሼህ መሐመድ አል-አሙዲ ለከተማዋ አስተዳደር ላበረከቱት ገንዘብ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕም፤ ዛሬ 20 ሚሊዮን ብር በብሔራዊ ደረጃ ለተቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ድጋፍ አድርጓል። (ኢዛ)



