Grand Ethiopian renaissance dam

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ

ኢትዮጵያ በአቋሜ እንደጸናሁ ነው ብላለች

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 6, 2020)፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌትን በተመለከተ ግብጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ አቤቱታው የሚለውጠው ነገር አለመኖሩን ገልጻለች።

ግብጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደብዳቤ ያቀረበችው አቤቱታ በጸጥታው ምክር ቤት እንዲታይላት በማሰብ ሲሆን፤ የአቤቱታዋ ጭብጥ የውኃ ሙሌቱ ላይ ያላትን ቅሬት የሚገልጽ እንደኾነ ተነግሯል።

ይህ የግብጽ አቤቱታ ግን በኢትዮጵያ ወገን ተቀባይነት የሌለውና የኢትዮጵያን አቋም አሁንም በሦስቱ የተፋሰሱ አገራት በጋራ ውይይት የሚፈታ መኾኑን በማመን፤ በቀደመው አቋሟ እንደጸናች መኾኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ