National Intelligence & Security Service (NISS), Ethiopia

ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል

ኢዛ (እሁድ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 10, 2020)፦ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በመጠቀም፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር (110 ሚሊዮን ዶላር) የማጭበርበርና ዘረፋ ወንጀል መክሸፉን አስታወቀ። እስካሁን አንድ ናይጄራዊ ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንደ ብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት መግለጫ፤ ተጠርጣሪዎቹ ነዋሪነታቸው ካሊፎርኒያ ግዛት በኾነውና ኒል ቻርልስ በተባለ ግለሰብ ስም በባንክ የተቀመጠ 110 ሚሊዮን ዶላር፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ለማውጣት ሲቀናጁ እንደነበር ይገልጻል።

ይህ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ዘረፋ፤ ወንጀሉ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ክትትል ስር ስለነበር፤ ትናንት ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በመጀመሪያ ዙር 60,990,939 (ስድሳ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠን መቶ ሠላሳ ዘጠኝ) ብር ከፊንፊኔ ቅርንጫፍ ጭነው ባዘጋጁት ተሽከርካሪ ሊወስዱ ሲሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ወንጀሉን ያቀናበረው አንድ ናይጄሪያዊ እንደኾነ የሚጠቀሰው ይኸው መረጃ፤ ናይጄሪያዊው የገንዘቡ ባለቤት ኒል ቻርልስ ነኝ ለማለት የሚያስችሉትን ሕገወጥ ሰነዶች በማዘጋጀት፤ የገንዘቡ ባለቤት ነኝ በማለትና በማስመሰል ከስድሳ ሚሊዮን ብር በላይ ከቅርንጫፉ በማውጣት፤ ከግብረአበሮቹ ጋር ገንዘቡን ባዘጋጅት መኪና ጭነው ከባንኩ ሳይወጡ በፊት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አስረደቷል። እስካሁን ይኸው ናይጄሪያዊና አምስት ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ