Nationa Museum of Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም

ከመጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተዘግቷል

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 10, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቀድመው አገልግሎት ማቋረጣቸውን ካስታወቁት የቱሪዝም መዳረሻ ተቋማት መካከል አንዱ የኾነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም፤ ከ200 ሺህ በላይ ጎብኝዎችንና ከቱሪስቶቹ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ማጣቱን አስታውቋል። ሙዚየሙ ከመጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተዘግቷል

የሙዚየሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹት፤ ብሔራዊ ሙዚየም ሰኔን ጨምሮ ባለፉት ሦስት ወራት ድረስ ከ200 ሺህ በላይ የውጭ ጎብኝዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ነገር ግን ከወረርሽኙ ሥጋት ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ወራትና በዚህ ወር በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ይጎበኛሉ ተብለው የተጠበቁትን የውጭ አገር ቱሪስቶችን ለማስተናገድ አልቻለም። ከእነዚህ ቱሪስቶች ይገኝ የነበረውም የውጭ ምንዛሪ መገኘት አለመቻሉ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ በቱሪስቶች ቀድመው ከሚጎበኙ ቦታዎች መካከል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን፤ በውስጥ ታሪካዊ ቅርሶች የአርኪዮሎጂ ውጤቶች ቅርፃ ቅርፆች እና ሌሎች ታሪካዊ መዛግብትን የያዘ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ