የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነገውን ስብሰባ ሰረዘ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነገውን ስብሰባ ሰረዘ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ያካሒድ የነበረውን ስብሰባ ሰረዘ

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 16, 2020)፦ ብሔራዊ ሙዚየም ለቀጣዮቹ አሥራ አምስት ቀናት ዝግ እንደሚኾን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በነገው ዕለት ሊያካሒደው የነበረውን መደበኛ ስብሰባ ሰርዟል።

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዛሬ እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ከነገ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ 15 ቀናት ለጎብኝዎች ዝግ ይኾናል።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ለአባላቱ ባስተላለፈው መልእክት፤ ነገ መጋቢት 8 ቀን ሊካሔድ የነበረው የምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ እንዳማይካሔድ አስታውቋል። ምክር ቤቱ ቀጣዩ ስብሰባ መቼ እንደሚካሔድ ወደፊት የሚያስታውቅ መኾኑንም በዚሁ መልእቱ ላይ ገልጿል።

የስብሰባውን መሰረዝ ምክንያት ያልተገለጸ በኾንም፤ አገሪቱ ውስጥ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ መኾኑ ይገመታል።

ምክር ቤቱ ሊወያይባቸው አቅዷቸው የነበሩት አጀንዳዎች ሦስት የነበሩ ሲሆን፤ እነሱም

1. የም/ቤቱን 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባዔ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣

3. የትራንስፖርት ሚኒስቴር የ2012 በጀት ዓመት የ7 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዳመጥ የሚሉት ነበሩ። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ