ኢሳይያስ አፈወርቂ ካርቱም ናቸው
የሱዳን የሽግግር መንግሥት ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂን ካርቱም ላይ አቀባበል ሲያደርጉላቸው
የኤርትራን እና የሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ላይ ይመክራሉ
ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 25, 2020)፦ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ካርቱም ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ሲሆን፤ በካርቱም የሦስት ቀናት ቆይታ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ፕሬዚዳንቱ በሱዳን ቆይታቸው የኤርትራን እና የሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ላይ የሚመክሩ ሲሆን፣ በቀጠናዊ ትብብር እና ውሕደት ዙሪያ ውይይቶችን እንደሚያደርጉም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። (ኢዛ)



