Hachalu Hundessa

አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ

ኢንጂንየር ይልቃል ታስረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 8, 2020)፦ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት፣ መቁሰል፣ ግምቱ ለጊዜው ላልታወቀ በርካታ ንብረት መውደም ምክንያት ከኾነው ኹከት ጋር በተገናኘ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ አመራሮችና የመንግሥት ኃላፊዎች እየታሰሩ ይገኛሉ። የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴን እና የከተማዋ አስተዳደርና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናደው አምቦ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ በመኾናቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

እነዚህ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሌሎችም የከተማ ባለሥልጣናት ተጠርጥረው የታሰሩበት ምክንያት፤ ከሌሎቹ ኹከቱ ከተነሳባቸው ከተሞች አንፃር ሲታይ በተለይ በሻሸመኔ ከተማ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡባት ከመኾንዋም በተጨማሪ፤ ከፍተኛ የንብረት ውድመት የተካሔደባት ከተማ እንደኾነች በተደጋጋሚ ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ባለሥልጣናቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው እንደኾነ ተነግሯል።

እንደሚነገረው ከኾነ በከተማይቱ ይሔንን ሁሉ ጉዳይ ያደረሰው የከተማዋ ነዋሪ እንዳልኾነና፤ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በፊት ከሌሎች ከተሞች የቀን ገንዘብ (ውሎ አበል መኾኑ ነው) እየተከፈላቸው፤ ከተማዋን የወረሩ ኃይሎች አደጋውን አድርሰዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ይህንን መረጃ ቀደም ብለው ያውቁ እንደነበርና እንዳልነበር እስካሁን ይፋ የወጣ መረጃ የለም።

የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች መታሰር

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር የኾኑት ኢንጂንየር ይልቃል ጌትነት በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን፤ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ለሐምሌ 11 ተለዋጭ ቀጥሮ ተሰጥቷቸውል። ኢንጂንየር ይልቃል በትክክል በምን ምክንያት ተጠርጥረው እንደታሰሩ የተረጋገጠ ነገር የለም።

የኦፌኮ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ) አባል የኾኑት አቶ ደረጀ ጣፋም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!