Jawar Mohammed (L) and Bekele Gerba (M)

አቶ ጃዋር መሐመድ (በግራ) እና አቶ በቀለ ገርባ (በቀኝ)

“አካውንቶቹ የታገዱት በሕጋዊ መንገድ ነው” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 31, 2020)፦ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በቅርቡ በተፈጠረው ቀውስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የእነአቶ ጃዋር መሐመድ የባንክ አካውንት መታገዱ ታወቀ።

የባንክ አካውንት እገዳው አቶ በቀለ ገርባንም ያካተተ ሲሆን፤ የሁሉቱም ተጠርጣሪዎች የቅርብ ቤተሰብ አካውንቶችም በተመሳሳይ መንገድ እንዲታገድ ተደርጓል።

የእነአቶ ጃዋር ጠበቆችና ቤተሰቦች የባንክ አካውንት የታገደው ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለመኾኑ ቢገለጽም፤ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ግን የባንክ አካውንቶቹ የታገዱት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ስለመኾኑ አስታውቋል።

ከአቶ ጃዋርና አቶ በቀለ ሌላ የጋዜጠኛ መለሰ ድሪባና የባለቤቱ የባንክ አካውንት ስለመታገዱም ለማወቅ ተችሏል።

በመረጃው መሠረት የአቶ ጃዋር መሐመድ እኅት ራዲያ ሲራጅ እና የአምስት ወንድሞቹ የባንክ አካውንቶች ስለመታገዳቸው ራዲያ ሲራጅ ለቢቢሲ ገልጻለች። እነዚህ ስድስት የባንክ አካውንቶች በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክና በአዋሽ ባንክ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

የአካውንት እገዳው የቤተሰብ አባሎችን ጭምር እንዲያጠቃልል የተደረገው ሕግ በሚፈቅደው መሠረት ምንጩን ለማረጋገጥ ስለመኾኑ ይጠቀሳል።

ነገር ግን እንዲህ ዐይነት የአካውንት እገዳዎች ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ የማይፈጸሙ በመኾኑ፤ የባንክ አካውንት እገዳው ሕጉን በጠበቀ መልኩ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ወጥቶ እንደኾነና ይህንን መመልከት እንደሚቻል ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ