እነአቶ ጃዋር ዳኛ ይቀየርልን ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ኾነ
አቶ ጃዋር መሐመድ (በግራ) እና አቶ በቀለ ገርባ (በቀኝ)
“አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም” ፍርድ ቤቱ
ኢዛ (ረቡዕ ነኀሴ ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 12, 2020)፦ እነአቶ ጃዋር መሐመድ በተከሰሱበት ክስ ጉዳያቸውን የሚያየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ይቀየርልኝ ብለው አቅርበውት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ኾነ።
የእነአቶ ጃዋርን አቤቱታ የተመለከተው በዛሬው ዕለት (ረቡዕ ነኀሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም.) የዋለው ችሎት፤ አቤቱታውን ውድቅ ያደረገው፤ አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ ባለመኾኑ ነው።
በዚሁ መሠረት እስካሁን የነበሩት ዳኛ የእነአቶ ጃዋርን ጉዳይ ማየት ይቀጥላሉም ተብሏል። (ኢዛ)



