Endrias Geta (PHD)

ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ፣ አዲስ የተሾሙት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳር

የዞኑ ምክር ቤት ለዶ/ር እንድሪያስ ጌታ ሹመቱን የሰጠው ዛሬ ባካሔደው ስብሰባ ነው

ኢዛ (ዓርብ ነኀሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 28, 2020)፦ በቅርቡ ከወላይታ ዞን አስተዳዳሪነታቸው በተነሱት በአቶ ዳጋቶ ኩምቤ ምትክ፤ ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ እንደተሾሙ ተገለጸ።

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ የተሾሙት የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ዓርብ ነኀሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሔደው ስብሰባ ነው።

አዲሱ ተሿሚ የዞኑ አስተዳዳሪ ኾነው ከመሾማቸው ቀደም ብሎ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመኾን ሲያገለግሉ እንደነበር ታውቋል።

የቀድሞው ዋና አስተዳዳሪ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ከሁለት ሳምንታት በፊት በዞኑ በተፈጠረው ኹከትና ኹከቱን ተከትሎ በደረሰው ጥፋት እጃቸው አለበት በሚል ነው።

ሕገወጥ እንቅስቃሴ አድርገዋል የተባሉት የቀድሞው አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከኃላፊነተቸው እንዲነሱ ተደርገው፤ በዛሬው ዕለት በምትካቸው አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሟል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ