የወላይታ ዞን

የወላይታ ዞን ተወካዮች ያቀረቡት አቤቱታ

ምክንያታቸው የወላይታ የክልል ጥያቄ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 15, 2020)፦ በደቡብ ክልል ውስጥ የክልል ጥያቄ ካቀረቡት ዞኖች መካከል አንዱ የኾነው የወላይታ ዞን ተወካዮች፤ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ለመቆየትም ኾነ በስብሰባ ለመሳተፍ የማይሹ መኾኑን አስታወቁ።

በደቡብ ክልል ምክር ቤት ወላይታን በመወከል በምክር ቤቱ ውስጥ አባል የኾኑት እኒሁ የወላይታ ተወላጆች፤ በክልሉ ምክር ቤት ለመቆየት የማይሹ መኾኑን ያስታወቁት የክልል ጥያቄያቸው በአግባቡ ሊስተናገድ ባለመቻሉ መኾኑን አስታውቀዋል።

ይህንን አቋማቸውን በገለጹበት ደብዳቤያቸው፤ “በክልል የመደራጀት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ በአፋጣኝ የክልሉ ምክር ቤት ስሕተቱን በማረም ይቅርታ ጠይቆ አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠ፤ ከእንግዲህ ሕገ መንግሥቱን እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አክብሮ የሕዝባችንን ጥያቄ በአግባቡ ማያስተናገድና የእኛን የምክር ቤቱን አባላት ደምፅ ለማስተናገድ ፈቃደኛ ባለኾነ ምክር ቤት ውስጥ አንሳተፍም” በማለት ገልጸዋል።

ይህንኑ ደብዳቤያቸውን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት፣ ለደቡብ ክልል መንግሥት ብሔረሰቦች ምክር ቤትና ለብልጽግና ፓርቲ ያሳወቁ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ በሚያካሒደው ስብሰባ ላይ ለመገኘት የማይገደዱ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል። የወላይታ ዞን በደቡብ ክልል ምክር ቤት ውስጥ 38 ተወካዮች አሉት። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ