Prof. Mesfin WoldeMariam

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

እንደ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው እንዲፈጸም ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ እየተጠበቀ ነው

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 2, 2020)፦ እውቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሥርዓተ ቀብር በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚፈጸም ተጠቆመ።

ከትናንት በስቲያ በኮሮና ቫይረስ በ91 ዓመታቸው ሕይወታቸው ያለፈው ፕሮፌሰር መስፍን የቀብር ሥርዓታቸው በክብር በመንግሥት እንዲፈጸም ጥያቄ ስለመቅረቡም ተነግሯል። እንደ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው እንዲፈጸም ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ እየተጠበቀበት ሲሆን፣ የሥርዓተ ቀብሩ ቦታም እስካሁን አልተወሰነም።

የፕሮፌሰርን ዜና እረፍት ተከትሎ የእርሳቸውን ስብእና የተመለከቱ አስተያየቶች እየተሰጡና የቀድሞ ቃለ ምልልሶቻቸው በተለያዩ የአገሪቱ መገናኛ ብዙኀን እየቀረበ ነው።

ኢዜማ ደግሞ የጽሕፈት ቤቱን ዋና የስብሰባ አዳራሽ መስፍን ወልደማርያም የስብሰባ አዳራሽ በሚል እንዲሰየም የኢዜማ ሥራ አስፈጻሚ ባካሔዱት አስቸኳይ ስብሰባ ወስነዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ለሕልፈት የበቁት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ሲሆን፣ ቫይረሱ ከቤት ሠራተኛቸው የተላለፈባቸው ስለመኾኑም ይነገራል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ