ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (በግራ)፣ ኢሰመኮ (መኻል)፣ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ (በቀኝ)

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (በግራ)፣ ኢሰመኮ (መኻል)፣ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ (በቀኝ)

“ፈር ቀዳጅ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነበሩ” ኢሰመኮ

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 2, 2020)፦ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በኢትዮጵያ ካሉት ታላቅ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኾነው በታሪክ ሲታወሱ እንደሚኖሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኮምሽኑ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ባወጣው የኀዘን መግለጫ፤ ፕሮፌሰር በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለመኾናቸው አስታውሷል።

ለበርካታ አሥርት ዓመታት የማይናወጥ ቁርጠኛ ሕይወት ከመግፋታቸውም በላይ፤ እስራትን የጨመረ ከባድ ዋጋ የከፈሉ ስለመኾናቸው በዚሁ መግለጫው ላይ አመልክቶ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የፕሮፌሰር መስፍንን ሕልፈት ተከትሎ ስለፕሮፌሰሩ፤ “ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አንጋፋ ምሁር፣ መምህር፣ የታሪክ አዋቂ እና ፖለቲከኛ ከመኾናቸውም በላይ፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጀግና ተብለው ለዘላለም የሚታወሱ፣ የማይፈሩ እና ቁርጠኛ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ነበሩ” በማለት ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ