TPLF letter to Dr. Arkebe Oqubay

ሕወሓት ለዶ/ር አርከበ እቁባይ የጻፈው ደብዳቤ

ለ27ቱ የሕወሓት የፓርላማ አባላትም ተመሳሳይ ጥሪ አስተላልፏል

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 5, 2020)፦ ሕወሓት በፌዴራል ደረጃ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ለሚገኙ 13 አባላቱና በፓርላማ የድርጅቱ አባል ናቸው ላላቸው 27 የፓርላማ አባላቱ፤ ኃላፊነታችሁን አቁማችሁ ለድርጅታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ሲል ጥሪ አስተላለፈ።

ዛሬ ሰኞ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሔደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም. የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተከናውኖ ሥራቸውን መጀመራቸውን ካስታወቁ በኋላ፤ ከሕወሓት ጽሕፈት ቤት ለድርጅቱ አባላት የተላለፈው መልእክት እያንዳንዱ ጥሪ የተደረገላቸውን የድርጅቱ አባላት ስም ዝርዝር በመጥቀስ ነው።

ጥሪውን ያስተላለፈበት ዋና ምክንያት፤ ከመስከረም 25 በኋላ ሕጋዊ መንግሥት ስላለመኖሩ በመጥቀስ ጭምር ሲሆን፤ ኃላፊነታችሁን ለቅቃችሁ ለድርጅታችሁ ሪፖርት አድርጉ ከተባሉት መካከል ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እና ዶ/ር አርከበ እቁባይ ይገኙባቸዋል።

ሕወሓት በፓርላማው ውስጥ 38 ወንበር ያለው በመኾኑ፤ ይህ ጥሪ የተላለፈው ለ27ቱ ነው። ቀሪዎቹ ስማቸው ያልተጠቀሰው እንደነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ያሉ የፓርላማ አባላት ቀድመው በፓርላማው መሳተፍ አቁመው መቀሌ ከመግባታቸው ጋርና ሕወሓት ለብቻው ባካሔደው ምርጫ ለክልሉ ምክር ቤት ተወዳድረው መቀመጫ ከማግኘታቸው ጋር የተያያዘ ነው ተብሎ ይገመታል።

ሕወሓት ዛሬ ማምሻውን ጥሪ ያስተላለፈበትን ሙሉ ቃል እንዲህ ገልጾታል። (ኢዛ)

በፌደራል ደረጃ፣ ድርጅታችን በመወከል ሲሠሩ ለነበሩ አመራሮችና የፓርላማ አባላት በተመለከተ የተላለፈ ውሳኔ

በፌደራል የሚገኘው ጥገኛና አምባገነናዊ ቡድን ሕገ መንግሥቱን በመጣስ ሥልጣኑን ማራዘሙ ተከትሎ ድርጅታችን ሕወሓት የዚሁ ኢ-ሕገ መንግሥታዊነት ተግባር አካል ስላይደለ ከመስከረም 25/2013 ዓ/ም ጀምሮ በፌደራል ደረጃ ምርጫን በማሸነፍ የሚያዙ ኃላፊነቶችና ውክልና የነበራችሁ የድርጅታችን አመራርና የፌደራል ፓርላማ አባላት ኃላፊነታችሁን በማስቆም ወደ ድርጅታችሁ ሕወሓት ሪፖርት እንድታደርጉ ውሳኔ የተላለፈ መኾኑን እናሳውቃለን።

ሀ/በፌደራል ደረጃ በድርጅታችን አቅራቢነት ሲሰሩ የቆዩ አመራሮች

1/ አምባሳደር ደ/ር አዲስዓለም ባሌማ
2/ ጓድ አፅብሃ አረጋዊ
3/ ዶ/ር ርከበ ዕቑባይ
4/ ጓድ አባይ ወልዱ
5/ ጓዲት ሮማን ገብረሥላሴ
6/ ጓዲት አልማዝ መኮነን
7/ ጓድ ተስፈአለም ይሕደጎ
8/ ጓድ ዶ/ር አብርሃም አዱኛ
9/ ጓዲት ምሕረት ምንአስቦ
10/ ጓድ ገብረትንሳኤ ገብረሚካኤል
11/ ጓዲት ሙሉ ገብረእግዚአብሔር
12/ ጓድ ገብረእግዚአብሔር አርኣያ
13/ ጓድ ዶ/ር ገረዜሄር ገ/ዮሐንስ

ለ/ በፌደራል የድርጅታችን ፓርላማ አባላት

1. አሰለፈች በቀለ ገ/ወልድ
2. ሽሻይ ኃ/ሥላሴ ወ/ስላሴ
3. አረጋዊ አፅብሃ ሓጎስ
4. ሹምዬ ገብሬ መኮነን
5. ግርማይ ሻዲ ክርቢት
6. አልማዝ አርአያ ገ/ሄር
7. ማና አብርሃ ወ/ማርያም
8. ሓድሽ አዛናው ገ/ዋህድ
9. ማሚት ተስፉ መድሃንዬ
10. ዊንታ ተኽሉ
11. ሓለፎም ግደይ
12. መብራት ገ/ጊወርጊስ አብርሃ
13. ልእልቲ ፀጋዬ አረጋዊ
14. ናፈቁሽ ደሴ አዛናው
15. ኪሮስ ወልደሚካኤል
16. አለምሰገድ ውሬታ ክፍሉ
17. ካሣ ጉጉሳ መንገሻ
18. አስቴር አማረ
19./ በርሀ ዝግታ ተስፋይ
20. ዮሐንስ በቀለ ገዛሀኝ
21. አበራሽ አድማሱ ገድሉ
22. ዳኘው በለጠ
23. ፅዋሃብ ታደሰ
24. አድሓና ሃይለ(ዶ/ር)
25. ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
26. ታደሰ አሰፋ
27. ያየሽ ተስፋሁነይ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ