ፍትሕ መጽሔት

ፍትሕ መጽሔት

የተፈቱት በራሳቸው ዋስ ሲሆን፤ ስትፈለጉ ትቀርባላችሁ ተብለዋል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 15, 2020)፦ ትናንት በፖሊስ ተይዘው ታስረው የነበሩት የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ዋና አዘጋጁ ምስጋን ዝናቤ ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።

በትናንትናው ዕለት (ረቡዕ ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም.) ከቢሯቸው ተይዘው የታሰሩት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩና ዋና አዘጋጁ ለእስር የበቁበት ምክንያት በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፤ መለቀቃቸው ታውቋል።

የእነ ጋዜጠኛ ተመስገንን እስር ቀድሞ በማኅበራዊ ሚዲያ የገለጸው የተመስገን ወንድም በዛሬው ዕለት መለቀቃቸውን ብቻ ነው ያመለከተው። ይህንንም “ጋዜጠና ተመስገን አሁን ተፈትቷል” በሚል ነው የገለጸው። ኾኖም መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነ ተመስገን የተፈቱት በራሳቸው ዋስ ሲሆን፤ ስትፈለጉ ትቀርባላችሁ ተብለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ