Journalist Temesgen Desalegn

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የመጽሔቱ ዋና አዘጋጁም በፖሊስ እጅ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 14, 2020)፦ የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቢሮዋቸው ተወስደው መታሰራቸው ተገለጸ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ወደ ቢሯቸው በመጡ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው የታሰሩበት ምክንያት ባይታወቅም፤ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ስለመኾናቸው ታውቋል።

ፖሊስ ከጋዜጠኛ ተመስገን ሌላ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤም ከቢሯቸው ተወስደው ስለመታሰራቸው ለማወቅ ተችሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ