National Bank of Ethiopia (NBE)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

አደጋ ሳያደርስ መጥፋቱ ተገለጸ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 15, 2020)፦ አዲሱን የብር ኖት በመቀየር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕንጻ ላይ እስከ አሁን መንሥኤው ያልታወቀ እሳት ተነስቶ እንደነበር ተገለጸ።

ባንኩ ካሉት ሦስት የቢሮ ሕንጻዎች አንዱ ላይ የእሳት አደጋው መድረሱን የሚጠቁመው መረጃ፤ የተነሳው የእሳት አደጋ ግን ምንም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር ውሏል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአሁኑ ወቅት የብር ኖት ቅያሬ ላይ የተወጠረ ሲሆን፤ አዲሱን ብር በማሰራጨትና አሮጊውን ብርም በመረከብ በእነዚህ ሕንጻዎች እያስቀመጠ ይገኛል።

ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. እሳት አደጋ ተነስቶ ነበረበት የተባለው የሕንጻው ክፍል፤ የተነሳው የእሳት አደጋ መንሥኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር ለውጡን ተከትሎ እስከ ሳምንቱ መጀመሪያ ድረስ 90 ቢሊዮን ብር አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨቱን እና 74.9 ቢሊዮን አሮጌውን ብር መሰብሰብ መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ