Danile Bekele (PHD), Ethiopian Human Rights Commission

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮምሽን ዋና ኮሚሽነር)

የሲቪል ሰዎች ደኅንነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ እና እየተባባሰ የቆየውን የትግራይ ክልል የጸጥታ ሁኔታ የሚያሳስበው መኾኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮምሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በሰጡት መግለጫ፤ አሁን በአካባቢው ያለው ሁኔታ የሚያሳስብ በመኾኑ ኮሚሽኑ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መኾኑን ገልጸዋል። ለፌደራል እና ለክልሉ የጸጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብአዊ መብቶችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲጠብቁና እንዲያከብሩ ጭምር ጥሪ ያስተላለፉት ዋና ኮሚሽነሩ፤ በተለይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ተፈጻሚ እንዲኾን የቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ረቂቅ አዋጅ መጽደቅ ላይ ለመምከር በሚሰበሰብበት በዛሬው ዕለት፣ ምግብና መድኃኒት የመሳሰሉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

እንዲሁም የግንኙነትና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ እንዳይቋረጥ ጥንቃቄ እንዲደረግ በማሳሰብ፣ የትግራይ ክልል በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደሚያስጠልልም አመልክተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ