Danile Bekele (PHD), Ethiopian Human Rights Commission

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

የሰዎች ሕይወት ከመጥፋቱ፣ የአካል ጉዳት ከመድረሱ፣ ንብረት ከመውደሙ፣ … በተጨማሪ፤ ክስተቱ የሕግ የበላይነትን የተፈታተነ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 30, 2019)፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ በተከሰቱት ኹከቶች የተሳተፉ አካላቶች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ አሳሰበ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ የተሾሙት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ወደዚህ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ እንደመጀመሪያ በሚጠቀሰው በዚህ በዛሬው መግለጫ፤ በኹከቱ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሳታፊ የኾኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ እንዳለበት አመልክቷል።

በኢትየጵያ የተጀመረው ለውጥና የተሃድሶ እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች እንዳስመዘገበ ሁሉ ውስብስብ ተግዳሮቶችም እየገጠሙት እንደሚገኝ የሚጠቁመው የኮሚሽኑ መግለጫ፤ ኹከቱ ካስከተለው ጥፋት ባሻገር የሕግ የበላይነትን በእጅጉ የተፈታተነ እንደኾነም ይጠቁማል።

ክስተቱ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ የጣለና እጅግ አሳሳቢ እንደኾነ ጠቁሟል። (ኢዛ)

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ