Samra Brouk and Alexander Assefa

ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሳምራ ብሩክ እና አሌክሳንደር አሰፋ

በኔቫዳና በኒው ዮርክ ሪፐብሊካንን አሸንፈዋል
ሳምራ ብሩክ በኒው ዮርክ የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሴናተር ኾናለች

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 7, 2020)፦ በአሜሪካ የዴሞክራት ፓርቲን ወክለው በሁለት የአሜሪካ ግዛቶች ለምርክ ቤት አባልነት እጩ ኾነው በመቅረብ የሪፐብሊካን ተፎካካሪዎቻቸውን አሸንፈዋል።

በኒው ዮርክ እና በኔቫዳ ግዛትቶች አሸናፊ የኾኑት ሁለቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሳምራ ብሩክ እና አሌክሳንደር አሰፋ ናቸው።

በተለይ በምርጫው አሸንፋ በኒው ዮርክ ሴናተር ለመኾን የበቃችው ሳምራ ብሩክ፤ በኒው ዮርክ የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሴኔት አባል ለመኾን ችላለች።

ሳምራ በኒው ዮርክ የተወዳደረችበት የምርጫ ጣቢያም ጥቁር ሴት ሲያሸንፍበት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

በዘንድሮው ምርጫ የዴሞክራት እጩ በመኾን በኔቫዳ ግዛት እጩ ኾኖ ያሸነፈው ሌላው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሌክሳንደር አሰፋ ነው። አሌክሳንደር በዚህ ግዛት ያሸነፈው ለሁለተኛ ጊዜ መኾኑ ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ