Muferiat Kamil

የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

ድጋፉን በማዕከል ለማድረግ ኮሚቴ ተዋቅሯል

ኢዛ (ረቡዕ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 11, 2020)፦ ለመከላከያ ሠራዊት እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ለማስተናገድ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን ያሳተፈ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙንና የመከላከያ ሠራዊት እያካሔደ ያለውን ሕግን የማስከበር ሥራ በመደገፍ ሕብረተሰቡ ፍቅርና ክብሩን እየገለጸ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህንን የገለጹት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያ ሠራዊቱ የጽንፈኛው የሕወሓት ቡድንን ወደ ሕግ ለማምጣት እያደረገ ባለው ጥረት ሕብረተሰቡ እያቀረበው ላለው የድጋፍ እናድርግ ጥያቄ የቀረበለት በመኾኑ ለዚህ ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይሁንታ መስጠቱን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በራስ ተነሳሽነት የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ሲሆን፣ በተለይ አንዳንድ ባለሀብቶች ሰንጋ በሬዎችን በመግዛት ድጋፍ እያደረጉ ጭምር ነው። ከጥቂት ቀናት በፊት ታዋቂው ነጋዴ አቶ በላይነህ ክንዴ 50 ሰንጋዎችን ያበረከቱ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው የመከላከያ ሠራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይል 100 የሥጋ በሬዎችንና 200 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸው ይጠቀሳል።

በጅማ ዞን የጌራ ወረዳ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የ28 ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውም ታውቋል። በተመሳሳይ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎችም ባለሀብቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የሚኾን ድጋፍ በተለያየ መንገድ እየተሰጠ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ