Sister Cecilia Gaudette መነኩሲት ሲሲሊያን በቴሌቭዥን መስኮት ሲናገሩ ይመልከቷቸው!  

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. October 14, 2008)፦ ነዋሪነታቸው ሮም የሆኑትና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሲስተር (መነኩሲት) ሲሲሊያ ጋውዴት የ106 ዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ፣ በዘንድሮው የአሜሪካን ምርጫ ድምፃቸውን ለሴናተር ባራክ ኦባማ እንደሚሰጡ ጣሊያን ሀገር ለሚታተም አንድ ጋዜጣ ቃለምልልስ ከሰጡ ወዲህ ታዋቂነትን አተረፉ። 

 

መነኩሲት ሲሲሊያ የተወለዱት በዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ በኒው ሐምፕሻየር ግዛት ውስጥ ሲሆን፣ ላለፉት 50 ዓመታት ነዋሪነታቸው በጣሊያን ሀገር ዋና ከተማ ሮም እንደሆነ ታውቋል።

 

ለመጨረሻ ጊዜ በምርጫ የተሳተፉት የዛሬ 56 ዓመት (1952 እ.ኤ.አ.) ለፕሬዝዳንት አይዘንሐወር ድምፃቸውን የሰጡ ጊዜ ነበር። መነኩሲት ሲሲሊያ በዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን፣ በዘንድሮው ምርጫ ድምፃቸውን ከሚሰጡት የዕድሜ ባለፀጋዎች ውስጥ አንዷ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

መነኩሲት ሲሲሊያ ምንም እንኳን የመስማት ችግር ቢኖርባቸውም ጋዜጦችንና ቴሌቭዥን በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚያገኙ ታውቋል።

 

ስለሴናተር ኦባማ ያላቸውን አስተያየት መነኩሲት ሲሲሊያ ሲገልጡ ”በአካል አግኝቼው አላውቅም፤ ነገር ግን ጥሩ የግል ሕይወት ያለውና ጥሩ ሰው ይመስላል። ይሄ የመጀመሪያው ነገር ነው። እናም ሀገር የመግዛት ችሎታ ይኖረዋል” ብለዋል።

 

ሲ.ቢ.ኤስ. ኒውስ ቴሌቭዥን ያቀረበውን ዘገባ ከዚህ በታች ያገኙታል። (በቪዲዮው መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ያሉት በጽሑፍ የተደገፉት መልዕክቶች የሲ.ቢ.ኤስ. ኒውስ አለመሆናቸውን ልንገልጽ እንወዳለን።) ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑት!

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ