ትግራይ ክልል፣ መቀሌ

ትግራይ ክልል፣ መቀሌ

የትግራይ ወጣት የተፈጠረውን የተስፋ እድል ይጠቀም ዘንድ ጥሪ ቀረበ

ኢዛ (ማክሰኞ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 29, 2020)፦ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ መቀሌ ሰማዕታት ሐውልት ውስጥ በሚገኘው የቀድሞው የሕወሓት ጽሕፈት ቤትን በመረከብ በትግራይ ሥራውን በይፋ ስለመጀመሩ ተገለጸ። የትግራይ ወጣት በክልሉ የተፈጠውን የተስፋ እድል ይጠቀም ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል በመቀሌ ጽሕፈት ቤት በመኾን በሰጡት መግለጫ ፓርቲያቸው ሥራውን በትግራይ ስለመጀመሩና ሌሎች ፓርቲዎችም በነፃነት በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብታቸውን ስለመጎናጸፋቸውም አመልክተዋል።

በትግራይ የተስፋ እድል ተፈጥሯል ያሉት አቶ ነብዩ፤ በተለይ ወጣቱ የዚህ እድል ተጠቃሚ ይኹን ብለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!