የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ባንኩ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ባንኮች ቀድሞ ሥራ ጀምሯል
ኢዛ (ማክሰኞ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 29, 2020)፦ በትግራይ ክልል የተቋረጠውን የባንክ አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ሲደረግ የቆየው ጥረት ተሳክቶ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ውስጥ ዛሬ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክልሉ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ካሉ ባንኮች ቀድሞ ዛሬ በመቀሌ ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፎቹን ሥራ ባስጀመረበት ወቅት፤ ቅርንጫፎቹ በተገልጋዮች ተጨናንቀው ታይተዋል።
ሌሎች ባንኮች እስካሁን በትግራይ ውስጥ ሥራ ያልጀመሩ ቢኾንም፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ መጀመር ግን፤ ነዋሪውን ያስደሰተ ኾኗል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ሁሉም የአገሪቱ ባንኮች በትግራይ ክልል ከ600 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉዋቸው ይታወቃል። (ኢዛ)



