የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች

“የጁንታው ርዝራዦች በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ በፈጸሙት ጥቃት፤ በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ተቋርጧል” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 17, 2021)፦ በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ዳግም ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ “የጁንታው ርዝራዦች በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ በፈጸሙት ጥቃት፤ በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ተቋርጧል” በማለት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጉዳዩ ላይ በሰጠው ተጨማሪ መረጃ፤ “የጁንታው ርዝራዦች አደጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ - መሆኒ - መቀሌ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረሱት ጥቃት፤ በክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል” ብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ