ጌታቸው ኢታና

የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር እና የኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ጌታቸው ኢታና

በርካታ የሕወሓት አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 24, 2021)፦ የሕወሓት ቡድን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ትርምስ ለመፍጠር አቅዶት የነበረው ሴራ እንደ ፍላጐቱ አለመሳካቱን የኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎች ገለጹ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር እና የኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ጌታቸው ኢታና ዛሬ (ረቡዕ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም.) በሰጡት መግለጫ ከሐዲው የጁንታ ቡድን በሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈጽመ በኋላ፤ በኦነግ ሸኔ አማካኝነት የኦሮሚያ ክልልን ለማተራመስ ብሎም፤ የአገሪቱን ሕልውና አደጋ ላይ ለመጣል የነበረው እቅድ በሕዝቡ፣ በጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ በክልሉ ልዩ ኃይል፣ በመደበኛ ፖሊስ እና በሚሊሻ በቅንጅት መክሸፉንም አስታውቀዋል።

መከላከያ ውድ ዋጋ ከፍሎ አገሩን ከሴረኞች እኩይ ዓላማ ማትረፍ በመቻሉ ክብርና ምስጋና ይገባዋል ያሉት ኃላፊው፤ ወደፊትም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተደብቀው የሚንቀሳቀሱትን ርዝራዦችን ለማስወገድ ከመከላከያ ጋር በጥምረት መሥራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

እንደ ክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ሕወሓት “ለፀረ ሰላሙ ኦነግ” የሥልጠናና የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጥ እንደነበር እና ሠራዊቱ በሕልውና ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅትም ኾነ በቅርብ ጊዜያት በጠላት ላይ በተወሰደው እርምጃ “ለፀረ ሰላሙ ኦነግ” ሥልጠናና የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ በርካታ የሕክምና አባላት በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸውን አስረድተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ