የዓድዋ ድል በድምቀት ተከብሯል

ኢትዮጵያውያን የ125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድምቀት ሲያከብሩ
የአጤ ምኒልክን ስም ላለማንሳት ያንገራገሩ ወገኖች የታዩ ቢኾንም፤ ድሉን በሚመጥን ሁኔታ በዓሉ ተከብሯል
ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 2, 2021)፦ የዘንድሮው 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል ከዚህ ቀደም አከባበሩ ለየት ባለ ሁኔታ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በድምቀት በዛሬው ዕለት (ማክሰኞ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም.) ተከብሯል።
የዘንድሮ የዓድዋ በዓል በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በምኒልክ አደባባይ እና በመስቀል አደባባይ የተከበረ ሲሆን፤ በዓሉ በተከበረባቸው አካባቢዎች ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታዳሚዎች የተገኙበት ነበር። ከአዲስ አበባ ውጭ በተለያዩ ከተሞች በዓሉ የዓድዋ ድል አድራጊ ጀግኖችን ባወደሰ የተለያዩ መልእክቶችን በማስተላለፍ የተከበረ ነው።
ከዚህ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ አሁንም የታሪክ ሽሚያ ውስጥ እና ታሪክን በተለያየ መንገድ በመተርጎም፤ የዓድዋ ጦርነትን በመምራት ለድል የበቁትን የአጤ ምኒልክ ስም ላለማንሳት ያንገራገሩ ወገኖች የታዩ ቢኾንም፤ ድሉን በሚመጥን ሁኔታ በዓሉ ሊከበር ችሏል። በዓሉ በተከበረባቸው ከተሞች የክልል ፕሬዝዳንቶች የተገኙ ሲሆን፤ ደሉን የሚያወድሰ ንግግሮች ያደረጉበት ነበር። (ኢዛ)
